የኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ከኦነግ ሸኔ እንቅስቀሴ ነፃ መሆናቸው ተገለጸ

0
265

ረቡዕ ነሐሴ 24 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የኦነግ ሸኔ ቡድን በስፋት ሲንቀሳቀስባቸው የነበሩ በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች የሚገኙ ስትራቴጂክ ሥፍራዎች ከቡደኑ የሽብር እንቅስቀሴ ነፃ መሆናቸውን የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አስታውቋል።

በሰራዊቱ ክፍሎች በተካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ ቡድኑ ኅብረተሰቡን ለመዝረፍ እና የትራንስፖርት መስመሮችን ለመዝጋት የሚጠቀምባቸው እንዲሁም፤ ለሽብር ሥራው ምቹ የነበሩ ቦታዎች በሰራዊቱ ነፃ ማድረግ መቻሉን ዘመቻውን በመምራት ላይ የሚገኙ ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮች ተናግረዋል።

በዚህም በሽብር ቡድኑ ላይ እየተወሰደ የሚገኘው የተቀናጀ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የተገለጸ ሲሆን፤ ሰራዊታቱ ለአገር እና ለህዝብ አስተማማኝ ሰላም የማስፈኑን ተግባር ጥበብ በተሞላበት ወታደራዊ ሳይንስ እንደሚፈጽምም ተገልጿል።

ለተዋጊው የሰራዊት ክፍሎች አስተማማኝ ድጋፍ በመስጠት ላይ የሚገኙት የክፍሉ ከባድ መሳሪያ ምድብተኞች በበኩላቸው፤ በኦነግ ሸኔ ላይ እየተወሰደ በሚገኘው ዘመቻ ላይ የተጣለባቸውን ሙያዊ ሃላፊነት በብቃት ከመወጣት ባሻገር የሚሰጣቸውን ማንኛውም ተልዕኮ በከፍተኛ ሞራል እና ተነሳሽነት በመፈፀም ላይ እንደሚገኙም ማብራራታቸውን ከሰራዊቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here