ፍትሕ ሚኒስቴር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 34 ሺህ 643 መዛግብት ዉሳኔ ማግኘታቸውን ገለጸ

0
234

ሐሙስ መስከረም 24 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር በዐቃቤያነ ሕግ እጅ ከነበሩ አጠቃላይ 36 ሺሕ 734 የምርመራ መዝገቦች ውስጥ፤ በ34 ሺሕ 643 መዛግብት ላይ የተለያዩ ውሳኔዎችን መስጠቱን ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል።

የፍትህ ሚኒስቴር የወንጀል ምርመራ በአራቱም የወንጀል ዓይነቶች ማለትም በኢኮኖሚ 2 ሺሕ 461፣ በድንበር ተሻጋሪ 751፣ በሙስና 628፣ በልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ደግሞ 32 ሺሕ 894 የምርመራ መዝገቦች መሆናቸውን ገልጿል።

በመሆኑም የምርመራ መዝገቦችን የማጥራት አፈጻፀም በእቅድ ተይዞ ከነበረዉ 84 በመቶ በአማካይ ወደ 94.3 በመቶ በማድረስ ከተቀመጠው እቅድ በ10.3 በመቶ ብልጫ ማስመዘግብንም አመላክቷል።

አፈፃፀሙ የተሻለ ቢሆንም በበጀት ዓመቱ ከቀረቡ መዛግብት ዉስጥ በተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ የወንጀል ጉዳዮች 2፣ በኢኮኖሚ ነክ ወንጀል ጉዳዮች 169፣ በሙስና ወንጀል ጉዳዮች 89 እና ልዩልዩ ወንጀል ጉዳዮች 1851 መዝገቦች በአጠቃላይ 2 ሺሕ 111 መዝገቦች ደግሞ ወደ 2016 የበጀት ዓመት የተላለፉ መሆናቸው ጠቁሟል።

በመሆኑ በቀጣይ ትኩረት ሰጥቶ መዛግብትን የማጥራት ሥራ መሰራት እንዳለበትም ተመላክቷል።

የፍትህ ሚኒስቴር በአዋጅ ከተሰጡት ዋነኛ ተግባራት ዉስጥ አንዱ የወንጀል ሕግ አፈፃፀም ዉጤታማነትን ማሳደግ ሲሆን፤ ተቋሙ በተጠናቀቀዉ የ2015 በጀት ዓመት ይህንኑ ተግባሩን ለማሳካት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት የተሻለ አፈፃጸም ማስመዝገቡንም ገልጿል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here