ሐሙስ መስከረም 24 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ በ#Choiseul100Africa በአፍሪካ የኢኮኖሚ እድገት ውስጥ ትልቅ ሚና ከሚጫወቱ 100 ወጣት አፍሪካዊ መሪዎች መካከል አንደኛ ደረጃን በመያዝ ተመርጠዋል።
“Choiseul 100 አፍሪካ” ልዩየሆነ በሿዘል ኢንስቲትዩት የሚደረግ ጥናት ሲሆን፤ አፍሪካን ወደ ከፍተኛ የኢኮኖሚ፣ የማህበረሰብ እና የባህል እድገት ደረጃ የማድረስ አላማ ያነገበና እድሜያቸው 40 እና ከዚያ በታች የሆኑትን 200 ወጣት የአፍሪካ መሪዎችን በመለየት እውቅና የሚሰጥ በፈረንሳይ የሚገኝ ተቋም ነው።
ኩባንያው ሽልማቱን አስመልክቶ ባሰራጨው መግለጫ፤ “…የሞባይል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠን፣ የዲጂታል እና የፋይናንስ አካታችነትን በማረጋገጥ ረገድ ላከናወናቸው እና እያከናወንን ላለናቸው ሥራዎችና ስለጥረታችን የተሰጠ አበረታች እውቅና መሆኑን በመገንዘብ ታላቅ ኩራት ይሰማናል” ብሏል።



