በያዝነው ወር በአዲስ አበባ የ20 ሺሕ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ይጀመራል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት ጽሕፈት ቤት በ2012 ግንባታቸውን ከሚያስጀምራቸው 150 ቤቶች ውስጥ ኹለተኛውን ዙር በ40 ቢሊዮን ብር ገደማ የ20 ሺሕ ቤቶችን ግንባታ በኅዳር ወር መጨረሻ እንደሚያስጀምር ታወቀ።

በመላው ከተማዋ በሚገኙ ክፍለ ከተማዎች 300 ሄክታር መሬት ቦታ ለግንባታው እየተመቻቸ ሲሆን፣ ይህ እንደተጠናቀቀም ከ 160 በላይ ተቋራጮችን ከኹለት ሺሕ ተቋራጮች መካከል በመምረጥ ወደ ሥራ እንደሚገቡ አዲስ ማለዳ ያገኘችው መረጃ ያሳያል። በመጪው ሳምንትም በዘጠኝ ክፍለ ከተሞች ላይ እንደሚገነቡ ይፋ የተደረጉትን የ20 ሺሕ ቤቶች ግንባታ ከ 168 ተቋራጮች ጋር ውል እንደሚፈጸም ጽሕፈት ቤቱ ለአዲስ ማለዳ ገልጿል።

‹‹የአጥር ሥራ እንዲሁም ብቁ ለተባሉ ተቋራጮች ግብዣ በማድረግ የገንቢዎች መረጣ ያከናወንን ሲሆን ውል ለማሰር የሚያስፈልጉ መስፈርቶችን ልከልናቸዋል፣ በመጪው ሳምንት የሚጠበቅባቸውን መስፈርት ካሟሉ በኋላ ውል አስረን በፍጥነት ወደ ሥራ እንገባለን›› ሲሉ የጽሕፈት ቤቱ ምክትል ሃላፊ ኪሮስ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

እያንዳንዱ ተቋራጭ አንድ ብሎክ የሚገነባ ሲሆን አንድ ተቋራጭ ኹለት ብሎኮችን ገንብቶ በአጠቃላይ በመጀመሪያው ዙር 169 ባለ ዐስር፣ 12 እና 21 ወለል ህንጻዎች እንደሚገነቡ ማወቅ ተችሏል። በኹለተኛው ዙርም ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸው ብሎኮች የሚገነቡ ሲሆን የተያዘላቸው በጀትም ተመሳሳይ መሆኑን ኪሮስ ጨምረው ገልጻዋል።

የከተማ አስተዳደሩ በቅርቡ 500 ሺሕ ቤቶችን ለመገንባት ከያዘው እቅድ ውስጥ 150 ሺሕ የሚሆነውን የከተማው የቤቶች ልማት የሚያከናውን ሲሆን፣ እነዚህም በ 20/80 እንዲሁም በ 40/60 ተመዝግበው ለሚጠባበቁ የከተማው ነዋሪዎች እንደሚሆን ተገልጿል። ከተማ መሃል ይገነባሉ ለተባሉት እነዚህ ቤቶች፣ የዲዛይን ክለሳውን አካሒዶ ማጠናቀቁን ይፋ ያደረገው የከተማ አስተዳደሩ፣ በአምስት የተለያዩ አማራጮች የ 500 ሺሕ ቤቶችን ግንባታ እንደሚያከናውን መግለጹም ይታወሳል።

የኪራይ እና የቀበሌ ቤቶችን ለመገንባት በኹለት ቦታዎች የፓይለት ፕሮጀክት የጀመረው የከተማ አስተዳደሩ፣ 25 ሺሕ የሚሆኑ ቤቶችን በ 75 ሄክታር ቦታ ላይ እንደሚገነባም አስታውቋል። በተጨማሪም 175 ሺሕ ቤቶችን በከተማ አስተዳደሩ፣ በፌዴራል እና በከተማዋ ባሉ የክልል መሥሪያ ቤቶች ለሚሠሩ የመንግሥት ሠራተኞች የሚገነባ ሲሆን፣ ይህም 500 ሄክታር መሬት ላይ ያርፋል። ከዚህ ውስጥ 20 በመቶው የማዘጋጀት ሥራዎች ተገባደዋል።

አቅም ላላቸው የከተማዋ ነዋሪዎችም 25 ሺሕ አፓርታማዎች የሚሠሩ ሲሆን፣ በኢግል ሂልስ የሚገነባው ለገሃር ፐሮጀክትም በዚህ መደብ ይጠቃለላል። ቀሪ 75 ሺሕ ቤቶች በተያዘው ዓመት በሪል እስቴት አልሚዎች የሚገነቡ እንደሆነም ለማወቅ

ቅጽ 2 ቁጥር 55 ኅዳር 13 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here