የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ

0
250

አርብ ጥቅምት 23 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡

በ2015 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣቸውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተማሪዎች የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡

በዚህም መሰረት በኹሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣ 180 ከ 600 እና 150 ከ500) የተቆረጠ መሆኑ ተመላክቷል።

ከላይ በተራ የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግሥት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በዚህም መሠረት፦
👉 የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች ከ700- 255 ያመጡ

👉 የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች ከ700 -234 ያመጡ

👉 የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች ከ600- 218 ያመጡ

👉 የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች ከ600 – 200 ያመጡ

👉 ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ700- 224 ያመጡ

👉 ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ700- 210 ያመጡ

👉 ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ600 – 192 ያመጡ

👉 ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ600 – 180 ያመጡ

👉 አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ700- 210 ያመጡ

👉 አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ700- 210 ያመጡ

👉 አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ  ተማሪዎች  ከ600 – 180  ያመጡ

👉 አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ600 – 180  ያመጡ

👉 ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ500 -150 ያመጡ

👉 ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ500 -150 ያመጡ መሆን አለባቸው ተብሏል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here