የቀድሞው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ተገኔ ጌታነህ ባደረባቸው ድንገተኛ ሕመም ዛሬ ኅዳር 22/2012 ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ከጥር 2001-2008 ለሰባት ዓመታት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት በመሆን ያገለገሉ ሲሆን፤ ትላንት አመሻሽ ላይ ባደረባቸው ድንገተኛ ሕመም ወደ ሕክምና የተወሰዱ ሲሆን ዛሬ ኅዳር 22/2012 ሕይወታቸዉ ማለፉ ታውቋል። የስርዓተ ቀብሩን የሚያሥፈፅም ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን የቀብር ስነ ስርዓቱም በክብር ፕሮቶኮል እንደሚፈፀም አዲስ ማለዳ ከጠቅላይ ፍርድ ቤት ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።



