የሰበታ እግር ኳስ ቡድን ከሜታ አቦ ቢራ ጋር የ 18 ሚሊዮን ብር ስምምነት ተፈራረመ

0
873

ሰበታ ከተማ እግር ኳስ ቡድን ለአራት ዓመታት የሚቆይ የ 18 ሚሊዮን ብር ስምምነት ከሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካ ጋር ተፈራረመ።
18 ሚሊዮን ብሩ በአራት ዓመታት ተከፋፍሎ የሚከፈል ሲሆን፣ በመጀመሪያው ዓመት 3.5 ሚሊዮን ብር፣ በኹለተኛው ዓመት 3 ሚሊዮን ብር፣ በሦስተኛው እና በአራተኛው ዓመት በእያንዳንዱ ዓመት አራት ሚሊዮን ብር የሚይዝ ይሆናል። በአይነት ከሚደረገው ድጋፍ በተጨማሪ፣ የእግር ኳስ ቡድኑ የሚጠቀምበት ሜዳ ጥገና በስፖንሰር ስምምነቱ መጀመሪያ ክፍል የሚከናወን እንደሚሆን ተገልጿል።
የስፖንሰር ድጋፉ ሰበታ እግር ኳስ ቡድንን ከማጠናከር በተጨማሪ ፋብሪካው የኢትዮጵያን እግር ኳስ ለማጠናከር እና እያደገ የመጣውን የእግር ኳስ ተመልካች ቁጥር ከግምት ውስጥ በማስገባት የተፈረመ እንደሆነም ተጠቅሷል።
ሜታ አቦ ቢራ ፋበሪካ በ 1967 በሰበታ ከተማ ውስጥ የተመሠረተ እና በቢራው ኢንዱስትሪ በርካታ ዓመታትን የቆየ ሲሆን፣ ዲያጂዮ ከተባለ ዓለማቀፍ የአልኮል መጠጥ አምራች ባለቤትነት ስር ይገኛል። ድርጅቱ ፋብሪካውን ለመግዛት 225 ሚሊዮን ዶላር ወጪ አድርጓል። እስከ አሁንም ከ119 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማስፋፊያ ሥራ ወጪ ተደርጓል።

ቅጽ 2 ቁጥር 58 ታኅሣሥ 4 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here