እየተተገበሩ ያሉ የህግ ማስከበር እንቅስቃሴዎችን ፖለቲካዊ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት እንደማይቀበለው የትግራይ ክልል አስታወቀ፡፡

0
510

የጊዜያዊ አስተዳደሩ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ባወጣው መግለጫ በክልሉ የተንሰራፋውን ስርአት አልበኝነት ለመከላከል እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን ፖለቲካዊ አውድ ለመስጠት የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ተቀባይነት የሌላቸው ናቸው ሲል ተቃውሞን አሰምቷል፡፡

ቢሮው በመግለጫው ወንጀል ተበራክቷል፣ግድያና አፈናም ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥሩ እያሻቀበ ነው፤ ይህን መከላከል ደግሞ የክልሉ መንግስት ሃላፊነትና ግዴታ ነው ያለ ሲሆን የግል ፖለቲካዊ ፍላጎትን ከመሰረታዊ የህግና ስርአት ማስከበር ሂደት ነጣጥሎ ማየት ያስፈልጋልም ብሏል፡፡

በየትኛው ህገወጥ ተግባርና የወንጀል ስራ ላይ የተሰማራ ተቋምም ሆነ ግለሰብ ለህግ ማቅረብ ተጠናክሮ ይቀጥላል ያለው የጸጥታ ቢሮው የደከመችና ያላገገመች ትግራይን ማየት የሚፈልጉ አካላት በሚነዙት ተራ አሉባልታ አንሸበርም ሲል በመግለጫው አብራርቷል፡፡

በቀጣይም በክልሉ በስፋት የሚስተዋሉትን የግድያ፣የዝርፊያና የእገታ ወንጀሎች በቶሎ በማስቆም ትግራይን ወደ ቀደመ ሰላሟ እንመልሳታለን ነው ያለው፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here