የጊዜያዊ አስተዳደሩ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ባወጣው መግለጫ በክልሉ የተንሰራፋውን ስርአት አልበኝነት ለመከላከል እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን ፖለቲካዊ አውድ ለመስጠት የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ተቀባይነት የሌላቸው ናቸው ሲል ተቃውሞን አሰምቷል፡፡
ቢሮው በመግለጫው ወንጀል ተበራክቷል፣ግድያና አፈናም ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥሩ እያሻቀበ ነው፤ ይህን መከላከል ደግሞ የክልሉ መንግስት ሃላፊነትና ግዴታ ነው ያለ ሲሆን የግል ፖለቲካዊ ፍላጎትን ከመሰረታዊ የህግና ስርአት ማስከበር ሂደት ነጣጥሎ ማየት ያስፈልጋልም ብሏል፡፡
በየትኛው ህገወጥ ተግባርና የወንጀል ስራ ላይ የተሰማራ ተቋምም ሆነ ግለሰብ ለህግ ማቅረብ ተጠናክሮ ይቀጥላል ያለው የጸጥታ ቢሮው የደከመችና ያላገገመች ትግራይን ማየት የሚፈልጉ አካላት በሚነዙት ተራ አሉባልታ አንሸበርም ሲል በመግለጫው አብራርቷል፡፡
በቀጣይም በክልሉ በስፋት የሚስተዋሉትን የግድያ፣የዝርፊያና የእገታ ወንጀሎች በቶሎ በማስቆም ትግራይን ወደ ቀደመ ሰላሟ እንመልሳታለን ነው ያለው፡፡



