ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን የነበሩት ሀጂ ኢብሳ ብቸኛ ወንድ ልጃቸው በሸኔ እንደተገለባቸው ገለፁ 

0
668

ቅዳሜ ሐምሌ 27 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ለረጅም ዓመት የገንዘብ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ቀጥሎም  የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ሀጂ ኢብሳ ብቸኛ ልጃቸውን ሸኔ እንደገደለባቸው ገለጹ።

አቶ ሀጂልጃቸው በሸኔ ስለመገደሉ በፌስቡክ ገፃቸው የፃፉ ቢሆንም መችና የት ልጃቸው እንደተገደለ በፅሁፋቸው አላሰፈሩም።

አቶ ሀጂ ኢብሳ በፌስቡክ ገጻቸው “የባለስልጣን ልጅ በመሆኑ ብቻ አንድ ወንድ ልጄን ሸኔ በጥይት ደብድባ ነጠቀችኝ ሲሉ ነው ሀዘናቸውን የገለጹት።

አቶ ሀጂ አክለውም “በመራር ሀዘኔ ከጎኔ የቆማችሁ  እናቶቼ፣አባቶቼ፣እህቶቼና ወንድሞቼ ብድራችሁ በዓለም ይመለስ።” ሲሉ በፌስቡክ ገጻቸው አስፍረዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here