በትግራይ ክልል የኤሌክትሪክ ሀይል መቋረጥን ተከትሎ ቤት ሰብረው የሚገቡ ዘራፊዎች መበራከታቸው ተሰማ 

0
361

ሐሙስ ነሐሴ 02 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ለ38 ቀናት የኤሌክትሪክ ሀይል መቋረጥ እንዳጋጠመ እና በዚህም የአካባቢው ነዋሪዎች ከፍተኛ ስጋት ላይ እንደወደቁ ተገልጿል፡፡

የኤሌክትሪክ ሀይል መቋረጡ ያጋጠመው ዋና ከተማዋን መቀሌን ጨምሮ በኀገረሰላም፣ ሰባካሪ እና ወይራድ በተባሉ የክልሉ አካባቢዎች ሲሆን በዚህ የሃይል መቆራረጥ የተነሳም ነዋሪዎች ቤት ሰብረው በሚገቡ ዘራፊዎች የደህንነት ስጋት እንዳደረባቸው አዲስ ማለዳ ከምንጮቿ ተረድታለች፡፡

ከዛም ባለፈ እንደ ምግብ ማብሰል ያሉ የእለት ተእለት ስራዎችን በማገዶ እንጨት እንዲጠቀሙ መገደዳቸውንም አስታውቀዋል፡፡

በክልሉ ያለው የኤሌክትሪክ ሀይል ማከፋፈያ ባጋጠመው ብልሽት ችግሩ የተፈጠረ ስለመሆኑም ተነግሯል፡፡

ክልሉ በድህረ ጦርነት ሂደት ላይ ያለ በመሆኑ በርካታ ማህበራዊና ኢኮኖሚዊ ቀውሶች እያስተናገደ ነው የሚሉት ነዋሪዎች አሁን ላይም በተከሰተው የሃይል መቆራረጥ ምክንያት በክልሉ አሳሳቢ ሆኖ የቀጠለው የዝርፍያ ወንጀል ተባብሶ መቀጠሉ ጠቁመዋል፡፡

እቃዎችን ወደ ሱቅ ወጥቶ መግዛት አሳሳቢ ነው ልጆቻችንም ድብደባ ይፈጸምባቸዋል፣ከዛም ባለፈ በቤታችን ቁጭ ባልንበት እንዘረፋለን ይህም አፋጣኝ መፍትሄ ያስፈልገዋል ሲሉ ነው ስጋታቸውን ያጋሩት፡፡

የክልሉ መንግስት በበኩሉ ከፌድራል መንግስቱ ጋር በመነጋገር በአጭር ጊዜ ውስጥ ክልሉ የሃይል አቅርቦት እንዲያገኝ እየተሰራ ስለመሆኑ ገልጿል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here