ታይም መፅሄት ትውልደ ኢትዮጵያዊውን ታዳጊ ሔማን በቀለን ‘የአመቱ ታዳጊ’ በማለት መረጠ 

0
261

ሐሙስ ነሐሴ 09 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ዝነኛው ታይም መፅሄት ዛሬ ይፋ ባደረገው መረጃ ወደፊት የቆዳ ካንሰርን ሊያድን የሚችል ሳሙናን ለመፍጠር አሜሪካ ውስጥ ምርምር እያረገ ያለውን ትውልደ ኢትዮጵያዊ ታዳጊ ሔማን በቀለን ‘የአመቱ ታዳጊ’ በማለት መምረጡን አስታውቋል።

አሁን የ15 አመት ታዳጊ የሆነው ሔማን ከ7 አመቱ ጀምሮ የተለያዩ ኬሚካሎችን በማቀላቀል ውጤቱን ማየት ያስደስተው እንደነበር የገለፀው መፅሄቱ አሁን ደግሞ አሜሪካን ሀገር ሜሪላንድ ግዛት ውስጥ ምርምሩን በስፋት እያከናወነ እንደሆነ ጠቅሷል።

ታዳጊው በቅርቡ ስሪ ኤም ኩባንያ ያዘጋጀውን አንድ ውድድር አሸንፎ የ25 ሺህ ዶላር ሽልማት እንዳገኘ ገልጿል።

ምርምሩ አመታትን ሊወስድ ቢችልም ሔማን በአሁን ወቅት በጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በሚገኘው የብሉምበርግ የህብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት ስራውን እያከናወነ ይገኛል።

“የቆዳ ካንሰርን ለማከም የሚደረጉ ምርምሮች ይስቡኛል” የሚለው ሔማን ወደፊት አንድ ቀን እሱ የሚሰራው ሳሙና የካንሰር በሽታውን ማከም እንደሚችል ማሰቡ እንደሚያስደስተው ገልጿል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here