ረቡዕ ነሐሴ 08 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የዝንጀሮ ፈንጣጣ (MPox) የዓለም አቀፍ አሳሳቢ የህዝብ ጤና ደኅንነት ስጋት እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት ወሰነ።
የዝንጀሮ ፈንጣጣ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና በአፍሪካ የሥርጭት መጠኑ እየጨመረ መምጣቱን የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም አሳውቀዋል።
ከዚህ ባለፈ፣ የዝንጀሮ ፈንጣጣን የአፍሪካ ሲዲሲ የህብረተሰብ ጤና አህጉራዊ ደህንነት ስጋት እንደሆነ ገልጿል።
በሌላ በኩል ፤ እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ የተያዘ ሰው አለመኖሩን የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ዛሬ አመልክቷል።
በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት እና ሞያሌን ጨምሮ በሌሎች የመግቢያ ቦታ ላይ የቁጥጥርና ማጣራት ስራ እየተሰራ ነው።
በሽታው እስካሁን ጎረቤት ሀገር ኬንያን ጨምሮ በ13 የአፍሪካ ሀገራት መከሰቱን እንዲሁም፣ 2 ሺህ 8 መቶ 63 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው እና 5 መቶ 17 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸዉን ሲዲሲ አስታውቋል።



