ቅዳሜ ነሐሴ 11 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረ/ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ በቀጣይ ከሀላፊነት ለመልቀቅ ማሰቧን በዛሬው ዕለት በብሔራዊ ቴሌቪዥን በነበረ ዝግጅት ላይ አሳውቃለች።
በፓሪሱ ኦሎምፒክ ውድድር “ ለጠፋው ውጤት የኢትዮጵያን ህዝብ በድጋሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ “ ስትል ረ/ኮሚሽነር ደራርቱ ተናግራለች።
ከሀላፊነት ትልቀቅ የሚል አስተያየት እየተደመጠ ስለመሆኑ እና በዚህ ላይ ሀሳቧን የሰጠችው ደራርቱ የኢትዮጵያን አትሌቲክስ እና ህዝብ የሚጠቅም ከሆነ ህይወት ከመስጠት ጀምሮ ምንም ከማድረግ ወደኋላ አልልም።”ብላለች።
ሀላፊነትን በተመለከተ “ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምርጫችን በቀጣይ ጥቅምት ወይም ህዳር ወር ላይ ነው ፣ አዲስ ፊት ታያላችሁ ብዬ አስባለሁ ህዝብ ከጠየቀ በደስታ ነው የማደርገው።”በማለት ተናግራለች።
በአንጻሩ በባንዲራው ስም ከሀላፊነት እንዲለቁ የተጠየቁት ዶ/ር አሸብር “ ከሀላፊነት አልለቅም “ ሲሉ ምላሽ መስጠታቸው አይዘነጋም።



