በሊቀመንበሩ የሚመራው ህወሃት፣ በህወሃት ስም እንዳይንቀሳቀሱ ብሎ ትላንት ያገዳቸው እነ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ተሰብሰበዋል

0
547

እሁድ ነሐሴ 12 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በመቀሌ ከተማ በህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ህወሓት) ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ በወቅታዊ የህወሓት የፓለቲካ ሁኔት ላይ ያተኮረ ውይይት እያካሄደ ነው።

በውይይት መድረኩ ላይ ” 14ኛው የህወሓት ጉባኤ ህጋዊ አይደለም ” ብለው የተቃወሙ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ፣ የድርጅቱ የማእከላዊ ቁጥጥር ኮሚሽን ፣ የክልል ፣ የዞን ፣ የወረዳና ሌሎች አመራሮች በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።

የህወሓት ምክትል ሊቀ-መንበር ጌታቸው ረዳ፥ ” የውይይት መድረኩ ህወሓትን ለማዳንና ትግራይን ወደ ነባራዊ ሁኔታዋ ለመመለስ ወሳኝ ነው ” ማለታቸውን አዲስ ማለዳ ከምንጮቿ ሰምታለች።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ትናንት ቅዳሜ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫቸው ጉባኤውን ያካሄዱት አካላት የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርን ለመንጠቅ እንቅስቃሴዎች ሊያደርጉ ይችላሉ ብለን እንጠብቃለን ብለው የትግራይ ፀጥታ ሃይሎች ስልጣን ለሚፈልጉ አካላት መሳርያ ሊሆኑ አይገባም ሲሉ ማሳሰባቸውን አዲስ ማለዳ መዘገቧ አይዘነጋም።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here