በሽግግር ፍትህ የወንጀል ጉዳዮች የሚታዩበት ልዩ አዋጅ ዝግጅት በ2 ወር ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ

0
234

ሰኞ ነሐሴ 13 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሽግግር ፍትህ ትግበራ ፍኖተ ካርታ ዝግጅት መጠናቀቁን ተከትሎ በሽግግር ፍትህ የወንጀል ጉዳዮች የሚታዩበት ልዩ አዋጅ በ2 ወር ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የሽግግር መንግስት ተቋማት ቅንጅታዊ አመራር አስታውቋል፡፡

ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቀው አዋጅ በሽግግር ፍትህ ውስጥ የሚታዩ የወንጀል ተግባራትን የመዳኘት ስልጣን ያለውን ችሎት ስልጣንና አሰራር የሚወስን ነው ተብሏል፡፡

የዚህ ልዩ ችሎት አዋጅ ዝግጅትም በጠቅላይ ፍርድ ቤት አስተባባሪነት የሚከናወን መሆኑን አዲስ ማለዳ ከሽግግር ፍትህ የተቋማት ቅንጅታዊ አመራር መድረክ ሴክሬተሪያት መግለጫ ለመመልከት ችላለች፡፡
‹
ሌላኛው የሽግግር ፍትህ ፖሊሲው ካስቀመጣቸው ጉዳዩች አንዱ የሽግግር የፍትህ ስልቶችን የሚተገብሩ ነጻ እና ገለልተኛ ተቋማት ለማቋቋም የሚያስፈልጉ የተለያዩ የሕግ ማዕቀፎችን የሚመለከት እንደሆነ ተገልጿል፡፡
‹
የእነዚህ ሕጎች መውጣት በፖሊሲው ላይ የተመላከቱ ዓላማዎችን ለማሳካት እውነትን ለማውጣት፣ እርቅ የሚወርድበትን አሰራር ለመመስረት እንዲሁም ተጠያቂነትን ለማስፈን ቁልፍ ሚና እንደሚኖረው ተጠቁሟል፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ሚያዚያ 9 ቀን 2016 በሚኒስትሮች ምክር ቤት መጽደቁ የሚታወስ ሲሆን በመንግስት በተለይም በአስፈጻሚው አካል በኩል መቋቋሙ ግን በብዙዎች ዘንድ ትችቶች እንዲነሱበት አድርጓል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here