በጉራጌ ዞን  ሁለት ህፃናት በጅብ ተበልተዉ ህይወታቸዉ አለፈ

0
483

ማክሰኞ ነሐሴ 14 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን እንደጋኝ ወረዳ እድሜያቸዉ የ8 እና  የ9 ዓመት የሆኑ ሁለት  ታዳጊ ህፃናት በጅብ ተበልተዉ ህይወታቸዉ ማለፉን የዞኑ ፖሊስ አስታውቋል።

በጉራጌ ዞን እንደጋኝ ወረዳ በወሌቾ ቀበሌ አንዦኔ ተብሎ በሚጠራ መንደር ድርሻዬ ኑረዲን የተባለ የ8 ዓመት ታዳጊ ነሐሴ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ሠዓት ገደማ በጅብ መበላቱን  ፖሊስ አስታዉቋል።

በተጨማሪም ትናንት ሰኞ ነሐሴ 13 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሠዓት  በወረዳው ሸውራ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጎምሻ ተብሎ በሚጠራ መንደር መድሐኒት ፀጋዬ የተባለች የ9 ዓመት ታዳጊ በጅብ ተበልታለች።

ታዳጊዋ ከሌሎች ጓደኞቿ ወንዝ ውሀ ልትቀዳ በሄደችበት በቀን አድፍጦ ይጠባበቅ በነበረ የተራበ ጅብ ተበልታ ህይወቷ ሊያልፍ መቻሉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ተናግረዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here