በትግራይ ክልል ፣ በመንግስት መስሪያ ቤቶች ጊዚያዊ አስተዳደሩ የማያውቀው ማንኛውም ሰብሰባ ማካሄድ እንደማይቻል የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

ረቡዕ ነሐሴ 15 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ፊርማ ለሁሉም የክልሉ የታችኛው መዋቅር የተላከው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው ጊዚያዊ አስተዳደሩ ከፈቀደው ውጪ ሌላ ስብሰባ ማካሄድ አይቻልም የሚል ይዘትን የያዘ ነው።

እንደ ኮሌራ በሽታ መከላከል፣ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው መመለስና የክልሉን ግዛታዊ አንድነት ማስከበር ፣የ2016 ዓ.ም በጀት መዝጋትና የ2017 ዓ.ም በጀት ማዘጋጀት ሌሎች ህዝባዊና መንግስታዊ እቅዶች የጊዚያዊ አስተዳደሩ መሆናቸው የጠቀሰው የስራ መመሪያው ከዚህ ውጪ የሚደረጉ ሰብሰባዎች የተያዘው እቅድ ስለሚጎዱ አይፈቀዱም ብሏል።

ከላይ ከተጠቀሱት እቅዶች ውጪ ማሰተናገድ የጊዚያዊ አስተዳደሩን ስራ በማደናቀፍ ተጠያቂነት የሚያስከተል መሆኑን በመግለጽ አስጠንቅቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here