ረቡዕ ነሐሴ 15 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል መምህር የነበሩት ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ፣ በኢትዮጵያ ፖለቲካ መድረክ ብቅ ብለው የሰላ ትችት በመስጠት ይታወቁ ነበር።
አዲስ አበባ ፈረንሳይ ለጋሲዮን ተወልደው ያደጉት ዶ/ር ደረጄ ዘለቀ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ላይ ስለማረፋቸው አዲስ ማለዳ ከቤተሰቦቻቸው አሰምታለች::
የዶ/ር ደረጄ ዘለቀ የቀብር ሥነ ስርዓት ነገ ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያን እንደሚፈፀም ተገልጿል።



