ሴናፍ ዋቁማ 6 ግቦችን በማስቆጠር ኮከብ ግብ አስቆጣሪ መሆን ችላለች::
ሙስ ነሐሴ 23 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች ቡድን ሴናፍ ዋቁማ ባስቆጠረችው ብቸኛ ግብ በመታገዝ ኬንያ ፖሊስ ቡሌትስን በፍፃሜ ጨዋታ ረተዋል::
ይህንንም ተከትሎ የሴካፍ ዞን ኳሊፋየር አሸናፊ ሆነዋል:: ከዚህም በተጨማሪ በካፍ የሴቶች ቻምፒዮንስ የሚያሳትፋቸውን ትኬት በመቁረጥ ታሪክ ሰርተዋል::
ሴናፍ ዋቁማ አዲስ አበባ ላይ በተካሄደው በዚህ ውድድር 6 ግቦችን በማስቆጠር ኮከብ ግብ አስቆጣሪ መሆን ችላለች::
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴካፋ ዋንጫን ሲያነሱ ይህ በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው:: ከዚህ በፊት ሁለት ጊዜ በሁለተኛ ደረጃነት ሲያጠናቅቁ አንድ ጊዜ ደግሞ ሶስተኛ በመሆን ጨርሰዋል::



