የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን ኬንያ ፖሊስ ቡሌትስን በፍፃሜ ጨዋታ አሸነፈ

0
255

ሴናፍ ዋቁማ 6 ግቦችን በማስቆጠር ኮከብ ግብ አስቆጣሪ መሆን ችላለች::

ሙስ ነሐሴ 23 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች ቡድን ሴናፍ ዋቁማ ባስቆጠረችው ብቸኛ ግብ በመታገዝ ኬንያ ፖሊስ ቡሌትስን በፍፃሜ ጨዋታ ረተዋል::

ይህንንም ተከትሎ የሴካፍ ዞን ኳሊፋየር አሸናፊ ሆነዋል:: ከዚህም በተጨማሪ በካፍ የሴቶች ቻምፒዮንስ የሚያሳትፋቸውን ትኬት በመቁረጥ ታሪክ ሰርተዋል::

ሴናፍ ዋቁማ አዲስ አበባ ላይ በተካሄደው በዚህ ውድድር 6 ግቦችን በማስቆጠር ኮከብ ግብ አስቆጣሪ መሆን ችላለች::

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴካፋ ዋንጫን ሲያነሱ ይህ በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው:: ከዚህ በፊት ሁለት ጊዜ በሁለተኛ ደረጃነት ሲያጠናቅቁ አንድ ጊዜ ደግሞ ሶስተኛ በመሆን ጨርሰዋል::

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here