ላለፉት አመታት በእስር ላይ የነበሩት የኦነግ ከፍተኛ አመራሮች ተለቀቁ

0
379

ሐሙስ ነሐሴ 30 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ባለፉት አራት አመታት እስር ላይ የነበሩት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከፍተኛ አመራሮች ተለቀቁ።

ከእስር የተለቀቁት አመራሮቹም :-

– አብዲ ረጋሳ፣
– ሚካኤል ቦረን፣
– ኬነሳ አያና፣
– ለሚ ቤኛ፣
– ዶክተር ገዳ ኦልጅረ፣
– ገዳ ገቢሳ እና
– ዳዊት አብደታ ሲሆኑ ማምሻውን ከእስርቤት በዋስ መለቀቃቸውን የግንባሩ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ለሚ ገመቹ ለአዲስ ማለዳ ገልፀዋል።

የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው አቶ ለሚ አክለውም በእስር ላይ ለነበሩ ለኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራሮች ድምጽ የሆኑትን በሙሉ አመስግነዋል።

አመራሮቹ ፍርድ ቤት እንዲፈቱ የሰጠው ትዕዛዝ ተፈጻሚ ሳይሆን ለአራት አመታት በዕስር ላይ ስለመቆየታቸው ተገልጿል።

የፓርቲው አመራሮች ከ2012 እና 2013 ዓ/ም ጀምሮ በኦሮሚያ ፖሊስ ተይዘው በዕስር ላይ የቆዩ ሲሆን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እንዲለቀቁ ተደጋጋሚ ጥሪ ሲያቀርቡ መቆየታቸው ይታወሳል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here