“ስምምነቱ ዓለም አቀፍ ውል ነው መከበር አለበት ” ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳይ

0
685

አርብ ጳጉሜ 1 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የሚታየውን ዋናው የልዩነት ነጥብ በፕሪቶሪያ ውል ላይ ያለ አመለካለት ነው ያሉት ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳይ ስምምነቱ ዓለም አቀፍ ውል ነው መከበር አለበት” ሲሉም በቅርቡ እኔ ነኝ ህጋዊ ህወሓት የሚለው የእነ ዶ/ር ደብረፅዮን ሃይልን ሸንቆጥ አድርገዋል።

ጄነራሉ ይህን የተናገሩት በማይጨው ከተማ በነበረ ውይይት ላይ ነው፡፡

የጄነራሉን ሃሳብ ያጠናከሩት የግዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ የፕሪቶሪያ ውል ለማፍረስ የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ ጦርነትን መጥራት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል በማለት አስጠንቅቀዋል።

ይህንን የጊዚያዊ አስተዳደሩ አመራሮች የሰላ ትችት ተከትሎ መልስ የሰጠው የነ ዶክተር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል ቡድን ህወሓት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት እንደማይደግፍ ተደርጎ እየቀረበ ያለው ሃሳብ ስም ማጥፋት ነው ” ሲሉ ኮንኗል ።

ህወሓት በፕሪቶሪያ ስምምነትና አተገባበር የፀና አቋም አለው ” ያለው ቡድኑ በጊዚያዊ አስተዳደሩ አመራሮች በኩል የሚሰጡ አስተያየቶችም መሰረተቢስና ሃቅን ያልተንተራሱ ናቸው ሲል ወቀሳ አቅርቧል።

በህወሃት ውስጥ ያለው ፖለቲካዊ ውጥረት አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ እነዚህ ቡድኖች የእርስ በእርስ መካሰሱንና መወቃቀሱን ወደ ህዝቡ በማውረድ ለዳግም ጦርነት እየገፋፉት ነው በሚልም የተለያዩ አካላት ስጋታቸውን እያስቀመጡ ነው፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here