በየወሩ በአማካኝ 560 ሰዎች በግጭት ምክንያት ህይወታቸውን እንደሚያጡ ተገለጸ

ቅዳሜ ጳጉሜ 02 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ)ሰላም እንዲሰፍን፣ ፍትሕና ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ 10 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ‘የሰላም ጥሪ’ ባቀረቡበት ወቅት ነው እነዚህ የግጭት አህዞች የተገለጹት፡፡

በአዲሱ 2017 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን፣ ፍትሕና ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ፤ የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልን ጨምሮ 10 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፤ የሰላም ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን በ2016 ብቻ በመላው ኢትዮጵያ ከ1,792 በላይ የግጭት ኩነቶች የተመዘገቡ መሆኑን ገልጸው በነዚህ ግጭቶችም በጥቅሉ ከ6,164 በላይ ሰዎች መሞታቸውን አንስተዋል።

ይህም ማለት በግጭቶች ሳቢያ ብቻ በየወሩ በአማካይ 560 ሰዎች የተገደሉበት ዓመት እንደነበር አመላክተዋል።

በአማራ ክልል፣ ኦሮሚያ እና ሌሎች ክልሎችም የዘፈቀደ እስሮች፣ በከተማዎች ውስጥ እና አቅራቢያ በሚደረጉ የተኩስ ልውውጦች ሳቢያ የሚፈጠር አለመረጋጋትና መሸበር፣ እንዲሁም እነዚህን ቀውሶች ያስከተሉት የኑሮ ውድነት እና ጫና በአገሪቱ ተባብሰው ተስተውለዋል ብሏል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here