ዓርብ መስከረም 10 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ይህንን ያሉት የቀድሞ የእናት ፓርቲ አመራር አቶ ዳዊት ብርሃኑ ናቸው፡፡
እኚህ ፖለቲከኛ ፖለቲካ እርሜ ነው ያሉት ምን ደርሶባቸው እንደሆነ ዝርዝር ማብራሪያ ባይሰጡም በግል ምክንያት ነው ሲሉ አጠር ያለ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በተለይም ይላሉ እኚህ የቀድሞ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ፣ ፓርቲው አንደኛ መደበኛ ጉባኤውን መጋቢት 30 ቀን 2015 ዓ/ም ባከናወነበት ወቅት በጠቅላላ ጉባኤው በሕዝብ ግንኙነት ከተመረጥኩ በኋላ የተሰጠኝን ኃላፊነት በአግባቡ ስወጣ ቆይቻለሁ ” ብለዋል።
በትብብር ፓርቲዎችም ዘንድ ባለኝ የፀሐፊነት ሚና የበኩሌን ድርሻ ስወጣ ነበር ” ነው ያሉት።
ምንም እንኳን ፓርቲው ከተመሠረተ ያስቆጠረው እድሜ አጭር ቢሆንም የቆየሁባቸው አራት አመታት በሀሳብ ልዕልና እና በሰለጠነ የሀሳብ ጉርብትና ብቻ ፖለቲካ መስራት የሚችሉ አባላትን ያፈራንበትም ወቅት ነበር ” ሲሉም አክለዋል።
ከዚህም በኋላ ዳግም በፖለቲካ አደባባይ እንደማይታዩ አቶ ዳዊት ብርሃኑ አስታውቀዋል፡፡



