በደብረፅዮን (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት በሽረ ህዝባዊ ውይይት እያካሄደ ነው

0
359

እሁድ ፣ መስከረም 12 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) ከሰሞኑ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ላይ መፈንቅለ ስልጣን ሊያደርግ ይችላል የተባለው በደብረፅዮን (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት በሽረ ከተማ ህዝባዊ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

ህወሓት በሽረ ከተማ እያደረገ የሚገኘው ህዝባዋ ውይይቱ ከትናንት መስከረም 11 እስከ 16 በሁሉም የትግራይ ክልል ከተሞችና ወረዳዎች ይካሄዳል የተባለው አካል መሆኑን አዲስ ማለዳ ከምንጮቿ ሰምታለች።

በእነ ደብረፅዮን (ዶ/ር) ቡድን የሚመራው ህወሓት ለ14 ቀናት ጉባኤ አድርጎ የጊዜያዊ አስተዳደሩን ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸውን ጨምሮ 16  ከፍተኛ አመራሮችን ከህወሓት ካበረረ በዃላ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር ውጥረት ውስጥ መግባቱ ይታወሳል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here