አዲስ ማለዳ ከየጤና ወግ የበጎ አድራጎት ተቋም ጋር በጋራ ለመስራት ተፈራረመች

0
294

ዓርብ መስከረም 10 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) አዲስ ማለዳ እና የጤና መረጃዎችን ተደራሽ በማድረግ የሚታወቀው የጤና ወግ የበጎ አድራጎት ተቋም ጋር በጋራ ለመስራት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ በጤና ጉዳዮች ላይ ማህበረሰቡ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የቻምፒዮን ኮሚዩኒኬሽንስ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ሳምሶን አሸናፊ እና የአዲስ ማለዳ የጤና ፕሮግራም አዘጋጅ ዶ/ር ብሩክ ገነነ እንዲሁም የጤና ወግ ተወካይ ዶ/ር ቃልኪዳን ካሳዬ የመግባቢያ ስምምነቱን በተፈራረሙበት ወቅት በኢትዮጵያ በስፋት የሚስተዋለውን የጤና እና የህክምና መረጃዎች እጥረት በመቅረፍ ቀላል እና ግልጽ በሆነ መንገድ ለማህበረሰቡ በጋራ ተደራሽ ለማድረግ መስማማታቸውን ገልጸዋል፡፡

ይህ በአዲስ መልክ የሚቀርበው ፕሮግራም ከማህበረሰቡ የሚነሱ ጤና ነክ ጥያቄዎችን በሰፊው በመዳሰስ ማብራሪያ የሚሰጥበት ዝግጅት እንደሚሆን የገለጹት ዶ/ር ቃልኪዳን ካሳዬ በመገናኛ ብዙሃን በኩል የጤና መረጃዎችን ማስተላለፍ አይነተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

የአዲስ ማለዳ የጤና ፕሮግራም አዘጋጅ ዶ/ር ብሩክ ገነነ በበኩላቸው አዲስ ማለዳ ከጤና ወግ በጎ አድራጎት ተቋም ባለሙያዎች ጋር በጋራ በመስራት ለማህበረሰቡ አስፈላጊ የጤና መረጃዎችን ግልጽ እና ቀላል በሆነ ሙያዊ ትንተና ተደራሽ መደረጉ ጥቅሙ የጎላ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በበጎ ፍቃደኛ የህክምና ባለሙያዎች የተቋቋመው የጤና ወግ ላለፉት 5 አመታት ለማህበረሰቡ አስፈላጊ እና ጠቃሚ የጤና መረጃዎችን ሲያደርስ የቆየ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ከ85 በላይ በጎ ፍቃደኛ የጤና ባለሙያዎችን በስሩ ይዟል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here