እሁድ መስከረም 26 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የክልል ከተሞች የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር ነዋሪዎች ገለጸዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ ምሽት 2:15 ላይ በተለይ በኮዬ ፈጬ ፣ ሰሚት ፣ የካ አባዶ ፣ ሃያት ፣ ሲኢሚሲ እና ቦሌ አራብሳ መጠነኛ የመሬት ንዝረት እንደነበር ነዋሪዎች ገልፀዋል።
በተለይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች በስጋት ወደ መሬት ወርደው እንደሚገኙ አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።
የመሬት መንቀጥቀጡ በአዳማ ከተማ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ ነዋሪዎች ከተቀመጡበት እስከመጣል የደረስ ንዝረት እንደነበር የአዲስ ማለዳ ባልደረባ በስፍራው ተመልክቷል።
በሌላ በኩል ከአዳማ ከተማ ቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው መተሃራ ከተማ ላይ በሬክተር ስኬል 4.9 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን አዲስ ማለዳ ከምንጮቿ ሰምታለች።



