እሁድ መስከረም 26 ቀን 2017 ( አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች የመሬት ንዝረት እንደነበር ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ምሽት ላይ በተለይ በኮዬ ፈጬ ፣ ሰሚት ፣ የካ አባዶ ፣ ሃያት ፣ ሲኢሚሲ እና ቦሌ አራብሳ መጠነኛ የመሬት ንዝረት እንደነበር ነዋሪዎች ገልፀዋል።
በተለይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች በስጋት ወደ መሬት ወርደው እንደሚገኙ አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።



