ወደ ኤርትራ ሲደረግ የቆየው መደበኛ የስልክ አገልግሎት ተቋረጠ

ሐሙስ መስከረም 30 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ የሚደረግ የመደበኛ ስልክ አገልግሎት መቋረጡን በርካታ ኤርትራውያን እየገለጹ ነው ተባለ፡፡

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነታቸውን ካደሱ በኋላ ያስጀመሩት የመደበኛ ስልክ አገልግሎት በተጀመረ በሰባት አመቱ መቋረጡ ተጠቁሟል፡፡

በመሆኑም ከመስከረም 28 ቀን 2017 ጀምሮ አገልግሎቱ መቋረጡን ኢትዮጵያ የሚኖሩ ኤርትራውያን መናገራቸው ተሰምቷል፡፡

የአገልግሎት እገዳው እንዲደረግ ያስተላለፈው የትኛው የሀገሪቱ መንስግስት እንደሆነ የማይታወቅ ሲሆን ኤርትራ ውስጥ የበይነ መረብ(ኢንተርኔት) አለመኖሩ በሌላ አማራጭ ሰው መገናኘት አለመቻሉ ችግሩን ማባባሱ ተመላክቷል፡፡

በኤርትራ እና ኢትዮጵያ ያለው ግንኙነት እየላላ ስለመምጣቱ እየተነገረ ቢሆንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነት ምንም የተቀየረ ነገር እንደሌላ እና በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተናግረው ነበር፤ የኤርትራ መንግስት ግን በጉዳዩ ምንም አይነት ምላሽ አልሰጠም፡፡

በአንጻሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሰጠው መግለጫ ከነሐሴ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ ወደ አስመራ የሚደረገውን በረራ ለማቆም መገደዱን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here