በአዋሽ ፈንታሌ ዛሬ ጠዋት ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ

0
246

እሁድ፣ ጥቅምት 3 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ዛሬ ከጠዋቱ 1 ሠዓት ከ37 ገደማ በአዋሽ ፈንታሌ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ሠማራ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት አደም አሊ እንደገለጹት÷ ዛሬ ጠዋት በአዋሽ ፈንታሌ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ እስከ አሁን የተለየ ጉዳት የለም፡፡

ቀደም ሲል በፈንታሌ ዛሬ ጠዋት ደግሞ በአዋሽ ፈንታሌ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን በመግለጽ÷ የሚመለከታቸው አካላት በነዋሪዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ አስፈላጊውን ሥራ እንዲያከናውኑ ጠይቀዋል፡፡

በተለይም ነዋሪዎችን ወደ ሌላ ቦታ የማዛወር ሥራን ጨምሮ ሌሎች የቅድመ ጥንቃቄ ተግባራትን ማከናወን እንደሚገባ መክረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ባለፈው ከተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝርት ቀጥሎ አሁንም ዳግም መከሰቱን ዶክተር ኤሊያስ ሊዌ አረጋግጠዋል።

ዛሬ ጠዋት 1:37 ደቂቃ ከ50 ሰከንድ ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት አዲስ አበባ ድረስ መሰማቱንም ተናግረዋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው ባለፈው በተከሰተበት አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ሲሆን በሬክተር ስኬል 4.6 አካባቢ እነደሆነም ዶክተር ኤሊያስ ሌዊ ለብሔራዊ ጣቢያው አረጋግጠዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here