የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ የልደት በዓል በጎንደር እየተከበረ እንደሚገኝ ተገለጸ

0
1095

የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ 201ኛ የልደት በዓል በጎንደር ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ እንደሚገኝ የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘገበ ።

”ጥምቀትን በጎንደር” የማክበር የባህል ሳምንት አካል ሆነው የአጼ ቴዎድሮስ ልደት ክብረ በኣል ከዛሬ ጥር 6/2012 ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች መከበሩ እንደሚቀጥል ታውቋል። የጎንደር ከተማ አስተዳደርም በተለይ ደግሞ በቴዎድሮስ እና በመስቀል አደባባዮች ዛሬ ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ በጎዳና ላይ ትርኢቶችና በስዕል ኢግዚቢሽን የልደት በዓሉን ማክበር እንደሚቀጥል አስታውቋል።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ማስተዋል ስዮም የአሁኑ ትውልድ ከቀደምት አባቶቹ ታሪክ ተምሮ የራሱን ታሪክ መስራት እና መገንባት እንደሚኖርበትም አስታውሰዋል።

የክብረ በዓሉ አንድ አካል ሆነው የፓናል ውይይት ላይ የጎንደር ዩኒቨርስቲ ምሁራን ከበኣሉ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ጽሑፎች አቅርበዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here