በዘንድሮ 2012 የመራጮች ምዝገባ ጊዜ ከመጋቢት 29-ሚያዝያ 28 እንደሚሆን ተገለጸ

0
528

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የ2012 አገራዊ የምርጫ መርሃ ግብርን ይፋ ባደረገበት ወቅት የመራጮች የምዝገባ ቀናት ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዚያ 28/2012 ለአንድ ወር የሚቆይ እንደሚሆን አስታወቀ። በአገራዊ መርጫ መርሃ ግብሩ ላይ እንደተገለፀው ከመራጮች ምዝገባም በተጨማሪ ለመራጮች ትምህርትና መረጃ የመስጫ ጊዜ የታወቀ ሲሆን ይህም ከመጋቢት14 እስከ ሚያዚያ 28 እንዲሆን ቀን ተይዞለታል።

ከመራጮች ምዝገባ ጋር በተያያዘም ከሚያዚያ 29 እስከ ግንቦት 8 2012 ድረስ የመራጮች ምዝገባ ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል ሲልም ምርቻ ቦርድ ዘግቧል። በዚሁ የአገራዊ መርጫ እጩዎች ከሚያዚያ 27 እስከ ነሐሴ 5/2012 ድረስ የምረጡኝ ቅስቀሳ ማድረግ የሚችሉ ሲሆን የዕጩ ምዝገባ  ቅሬታዎችም ሆኑ አቤቱታዎችም ከሚያዚያ 13 እስከ ግንቦት 30 ድረስ መቅረብ እንደሚኖርባቸው ቦርዱ ይፋ ባደረገው መርሃ ግብር አስታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here