በኹለት ሳምንት ውስጥ ብዛታቸው 11 የሆኑ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ አንድ ሺሕ የሚጠጉ የሌሎች አገራት ዜጎች፣ ሕጋዊ ሆነው ሳለ ፈቃድ ከተሰጣቸው የሥራ መስክ ውጭ በመሰማራታቸው መታሠራቸው ተገለጸ፡፡
ይህን አስመልክቶም በጅዳ ቆንስል ጀነራል አብዱ ያሲን እንደገለጹት፣ የሳውዲ መንግሥት በወሰደው እርምጃ 11 ኢትዮጵያውያን ተይዘዋል።
ሳውድ አረቢያ ከሰሞኑ ሕጋዊ ሆነው በምድሯ እየኖሩ ያልተፈቀደላቸውን ሥራ የሚሠሩ የተለያዩ አገራት ዜጎችን ማሰር መጀመሯ የተሰማ ሲሆን፣ በሕጉ መሠረት አንድ የውጭ ዜጋ ወደ ሳውዲ ሲገባ እንዲሠራ በተፈቀደለት የሥራ መስክ የማይሠራ ከሆነ እንደ ሕገወጥ ይቆጠራል ሲል ዶቸቬለ ዘግቧል።



