ፖምፒዮ ኢትዮጵያ በህዳሴ ግደብ ዙሪያ ከአሜሪካ ጫና እየተደረገባት አይደለም አሉ

0
700

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ መንግሥታቸው በታላቁ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ዙሪያ ኢትዮጵያ ከግብፅ እና ከሱዳን ጋር እያደረገቸው ባለው ድርድር ጫና እያደረገ እንዳልሆነ አስታወቁ።

በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን ከስምምነት ለመድረስ  ወደ ጫፍ የደረሱ ቢመስሉም ቀሪ ሥራዎች መሠራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

አሜሪካ ለግብፅ ትደግፋለች ተብሎ ለተነሳላቸው ጥያቄም፣ ፖምፒዮ አገሪቱ ሦስቱንም አገር ለመጥቀም እንደምትሠራ በመግለፅ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕም አገራቱ እኩል ተጠቃሚ ለማድረግ እየሠሩ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ፖምፒዮ አክለውም በግድቡ ዙሪያ በቅርቡ ከስምምነት ላይ እንደሚደረስ ተስፋ አለኝ ብለዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የነበራቸውን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ ረቡዕ የካቲት 11/2012 አጠናቀዋል፡፡

 

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here