በሳውድ አረቢያ ከተሰጣቸው የሥራ መስክ ውጪ ሲሠሩ የነበሩ 11 ኢትዮጵያውያን ተያዙ

0
318

 

በኹለት ሳምንት ውስጥ ብዛታቸው 11 የሆኑ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ አንድ ሺሕ የሚጠጉ የሌሎች አገራት ዜጎች፣ ሕጋዊ ሆነው ሳለ ፈቃድ ከተሰጣቸው የሥራ መስክ ውጭ በመሰማራታቸው መታሠራቸው ተገለጸ፡፡

ይህን አስመልክቶም በጅዳ ቆንስል ጀነራል  አብዱ ያሲን እንደገለጹት፣ የሳውዲ መንግሥት በወሰደው እርምጃ 11 ኢትዮጵያውያን ተይዘዋል።

ሳውድ አረቢያ ከሰሞኑ ሕጋዊ ሆነው በምድሯ እየኖሩ ያልተፈቀደላቸውን ሥራ የሚሠሩ የተለያዩ አገራት ዜጎችን ማሰር መጀመሯ የተሰማ ሲሆን፣ በሕጉ መሠረት አንድ የውጭ ዜጋ ወደ ሳውዲ ሲገባ እንዲሠራ በተፈቀደለት የሥራ መስክ የማይሠራ ከሆነ እንደ ሕገወጥ ይቆጠራል ሲል ዶቸቬለ ዘግቧል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here