ድንበር ላይ የሚደረጉ ተደጋጋሚ ፍተሻዎችን የሚያስቀር አሰራር ሊተገበር ነው

0
302

በኢትዮጵያና በሌሎች የጎረቤት አገራት ድንበር ላይ የሚደረገዉ ፍተሻ ተገልጋዮችን የሚያጉላላ እና ለተጨማሪ ወጪ የሚዳርግ በመሆኑ አዲስ የፍተሸ ስርዓት ተግባራዊ ለማድረግ የጉምሩክ ኮሚሽን እየሠራ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎች የአፍሪካ አገራት በአንድ የሚያልቅ የፍተሻ አገልግሎት ለማስጀመር በዝግጅት ላይ መሆኑን የገለፀ ሲሆን፣ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ተሽከርካሪዎች አንድ ጊዜ ብቻ ፍተሻ እንዲደረግባቸው የሚያደርግ ነው።

ከዚህ ቀደም የነበረዉ አሠራር በኢትዮጵያና በኬንያ እንዲሁም በጅቡቲ እና ሌሎች የአፍሪካ አገራት ድንበር አቋርጠዉ የሚገቡና የሚወጡ ተሽከርካሪዎች የሚደረገዉ ፍተሻ በሚገቡበት እና በሚወጡበት አገር ኹለት ጊዜ ፍተሻ እንዲያደርጉ የሚያስገድድ በመሆኑ አገልግሎት ፈላጊዎች ለመጉላላትና ለተጨማሪ ወጪ ሲዳርጋቸዉ እንደነበር ተገልጿል።

በመሆኑም ይህ የአሠራር ስርአት በኢትዮጵያና በሌሎች የአፍሪካ አገራት የሚደረገዉ የንግድ እንቅስቃሴ፣ ቀልጣፋና ምቹ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ይጠበቃል።
ኢትዮጵያ የአንድ አለቅ የፍተሻ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ጣቢያ በኢትዮ-ኬንያ ድንበር የገነባች ሲሆን፣ በቅርቡ ወደ ሥራ እንደሚገባ ታውቋል።

የአንድ ጊዜ ፍተሻ አገልግሎት የአሰራር ስርዓት በተለይም ወደብ የሌላቸዉ የአፍሪካ አገራት ቀልጣፋና ምቹ የንግድ እንቅስቃሴ እንዲኖራቸዉ ያስችላልም ተብሏል። ይህንን የአሠራር ስርዓት አስመልክቶ በተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ የጉምሩክ ጣቢያ ሠራተኞችም ሥልጠና በመስጠት ላይ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 68 የካቲት 14 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here