ኹለተኛዉ የፈርኒቸር፣ ቤተ ውበት እና ግንባታ ማስዋብ አዉደ ርዕይ ሊካሄድ ነው

0
689

የአገር ውስጥ እና ውጭ አገራት ድርጅቶች ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችልና ለፈርኒቸር ምርት አቅራቢ ድርጅቶች በጋራ ለመሥራት የሚያስችል አውደ ርዕይ ሊካሄድ ነው።

ኹለተኛዉ የፈርኒቸር፣ ቤተ ውበት እና ግንባታ ማስዋብ አውደ ርዕይ እና ጉባዔ ከየካቲት 26 እስከ የካቲት 28 ቀን 2012 ለኹለተኛ ጊዜ በሚሊንየም አዳራሽ ይካሄዳል።

አውደ ርዕዩ ለፈርኒቸር ምርት አቅራቢ ድርጅቶች የገበያ ትስስር ለመፍጠር ያስችላል የተባለ ሲሆን፣ ከ50 በላይ የአገር ውስጥ እና የውጭ አምራቾች፣ አቅራቢዎች እንዲሁም የፈርኒቸር ኢንዱስትሪ አምራቾች እየተሳተፉበት ይገኛሉ።

ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የኬሚካል እና ኮንስትራክሽን ግብይቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት እንዲሁም የፌዴራል አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስትሪ ልማት ኤጀንሲ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለአውደ ርዕዩ ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል።

ኢትዮጵያ በዓመት ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ሊያመነጭ የሚችል እና ለ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሰዎች የሥራ እድል መፍጠር የሚያስችል ገበያ ያላት ሲሆን፣ የአፍሪካን 67 በመቶ እንዲሁም በዓለም 7 በመቶ የቀርከሃ ሀብት ባለቤት ናት።

በምሥራቅ አፍሪካ 2ኛ ግዙፍ ፈርኒቸር ገበያ እንዲሁም በአፍሪካ 5ኛ የውጭ አገራት የፈርኒቸር ምርቶች መዳረሻ ነች። አውድ ርዕዩ ቤተ ውበትና የግንባታ አጨራረስ ምርቶች የገበያ ሰንሰለት ላይ የተዘጋጀ ሲሆን፣ በእንጨት ሥራ፣ በቤት፣ በቢሮ እና በኢንዱስትሪ ፈርኒቸሮች እንዲሁም የውስጥ እና የውጭ ማስዋቢያ ምርቶች፣ መብራቶች፣ መጋረጃዎች እና ልዩ ልዩ ግብዓቶች ላይ ትኩረት ያደረገ እንደሆነ አውደ ርዕዩ አዘጋጅ ፊንቴክስ ፉርኒቸር አስታዉቋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 69 የካቲት 21 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here