የሶማሌ ክልል ምክትል ፕሬዘዳንት ሙስጠፌ ዑመር መሐመድ ታናሽ ወንድም የሆኑት አብዲራህማን ዑመር በደገሃቡር ከተማ በደረሰባቸው በስለት የመወጋት አደጋ ለከፍተኛ ህክምና ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገቡ።
የፕሬዝዳንቱ ኮሚኒኬሽን አማካሪ መሐመድ ኦላድ ጥቃቱ የደረሰባቸው በትላንተናው እለት መሆኑን ገልፀው ለግዜው የጤንነታቸው ሁኔታ ላይ እና የጥቃቱን ምክኒያት በተመለከተ ማብራሪያ መስጠት እደማይችሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።



