ምርጫ ቦድር የተለያዩ የመንግሥት ተቋማትን ማብራሪያ ጠየቀ

0
703

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፓርቲዎች ለቀረቡለት አቤቱታዎች የተለያዩ የመንግሥት ተቋማትን ማብራሪያ ጠየቀ።

ቦርዱ  በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ፓለቲካ ፓርቲዎች ከመመዝገብ በተጨማሪ የተለያዩ ድጋፎችን እንደሚያደርግ በማስታወቅ ከሰሞኑን ከተለያዩ ፓርቲዎች የቀረበለትን አቤቱታ አስመልክቶ ምላሾችን መስጠቱንም አስታውቋል።

አቤቱታ ያቀረቡ ፓርቲዎች እና ያቀረቧቸው አቤቱታዎችም
– ትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ትዴፓ/- እስር፣ ማስፈራራትና ቢሮ መዘጋት
– ኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ/ኢዜማ/- ስብሰባዎች መሰናከል፣ በጎንደር በደብረብርሃን እና የጸጥታ ሃይሎች   ለመሰናከሉ ትብብር ማድረጋቸው
– ኦሮሚያ ብሔራዊ ፓርቲ/ኦብፓ/- እስራት፣ ቢሮ መዘጋት፣ ታፔላ መነቀልና አባላት ማስፈራራት
– ኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ/ኦፌኮ/- የአባላት እስርና ማስፈራራት
– ኦሮሞ ነጻነት ግንባር/ኦነግ/- የመስራቾች ፊርማ መነጠቅ እና በተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች የአባላት እስር
– ጌዲዮ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት/ጌህዴድ/- ሰነድ መነጠቅና የማሟያ ፊርማ ማሰባሰብ ሂደት መደናቀፍ

ሲሆኑ ፓርቲዎቹ ያቀረቡትን አቤቱታ በማያያዝ የሚመለከታቸውን የመንግስት አካላት ጉዳዩን ከሚያስረዱ ሰነዶች ጋር የካቲት 26 እና 27 ቀን 2012 ዓ.ም በቦርዱ ጽህፈት ቀርበው እንዲያስረዱ ደብዳቤ መላኩን ገልጿል።

ለአቤቱታዎቹ ምላሽ እንዲሰጡ ጥሪ የደረሳቸው ተቋማትም

– የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር
– ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር
– አማራ ፖሊስ ኮሚሽን
– ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ፖሊስ ኮሚሽን
– ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን
– ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ፣ ዝዋይ ባቱ ፖሊስ መሆናቸውን የአትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here