የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ መጋቢት 03/2012 በነበረው መደበኛ ስብሰባ የቀድሞ የገቢዎች ሚኒስትር የነበሩት አዳነች አቤቤን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሆነ መሾማቸውን አፀደቀ።
ከአዳነች አቤቤ በተጨማሪ ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የቀረበለትን የተለያዩ የሚኒስትሮች ሹመትን ተቀብሎ ያጸደቀ ሲሆን ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) የጤና ሚኒስትር ፣ ላቀ አያሌው የገቢዎች ሚኒስትር፣ ፊልሰን አብዶላሂ የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡



