ዳሰሳ ዘ ማለዳ መጋቢት03/2012

0
632

 

የገንዘብ ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚውል 300 ሚሊዮን ብር አጸደቀ

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የገንዘብ ሚኒስቴር፣የጤና ባለሙያዎች ለማሰልጠን፣አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ለሟሟላት እና ለህክምና ማዕከላት የሚውል 30 ሚሊዮን ብር አጸደቀ።

የጤና ሚኒስቴርም ቫይረሱን ለመከላከል የተመደበለትን ገንዘብ  እንሚጠቀምበት ተነግሯል።

የዓለም የጤና ድርጅት ኮሮና ቫይረስ ዓለም አቀፍ ወረርሽ መሆኑን በትላትናው ዕለት ማስታወቁም የሚታወስ ነው። (ፎርቹን)

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………..

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሁለት ሹመቶችን መስጠታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል። ከመጋቢት 1/2012 ዓ. ጀምሮ ወ ሕይወት ሞሲሳ የብረታ ብረት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር፤ ሜጀር ጄነራል አህመድ ሀምዛ ደግሞ የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል። (ጠቅላይ ሚንስትር ጽኅፈት ቤት)

…..………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………..

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ መጋቢት 03/2012 በነበረው መደበኛ ስብሰባ የቀድሞ የገቢዎች ሚኒስትር የነበሩት አዳነች አቤቤን  የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሆነው መሾማቸውን አፀደቀ።ከአዳነች አቤቤ በተጨማሪ ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የቀረበለትን የተለያዩ የሚኒስትሮች ሹመትን ተቀብሎ ያጸደቀ ሲሆን ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) የጤና ሚኒስትር ፣ ላቀ አያሌው የገቢዎች ሚኒስትር፣ ፊልሰን አብዶላሂ የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር  ሆነው ተሹመዋል።(አዲስ ማለዳ)

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………..

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባው የሚኒስትሮችን፣ የኮሚሽነርና የቦርድ አባላት ሹመትን ያጸደቀ ሲሆን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ቦርድ አባልነት የቀረቡት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላይ ያላቸውን ተቃውሞ አሰምተዋል። ቅሬታ ያቀረቡት  የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እንዳሉት ከሆነም  ግለሰቡ የሀይማኖት እኩልነት ላይ የማያምኑ፣ በዜጎች መካከል ክፍፍል እንዲፈጠር የሚሰሩ፣ በማለት በሕዝብ የሚነሱባቸው ቅሬታ ወደ ጎን በመተው መቅረብ አልነበረባቸውም በሚል አባልነታቸውን ተቃውመዋል።(ቢቢሲ አማርኛ)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………..

በድሬደዋ ገንደ ሮቃ አካባቢ የሰፈረው የጅብ መንጋ ከዚህ ቀደም የተከሰተ ሲሆን አሁንም ድረስ መንጋው እዘናጋ በጨቅላ ሕጻናት ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው ተብሏል።በየካቲት ወር ላይም የሁለት እና የሦስት ዓመት እድሜ ህጻናት በመንጋው ሕይወታቸውን ማልፉ ተገልጿል፡፡የጅብ መንጋውን ከሰረበት ለማባረር ጥሻ እና ዋሻዎች ማጽዳት ከተጀመረ አንድ ወር አስቆጥሯል።(ኢዜአ)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………..

በፌደራል ፖሊስ አዘጋጅነት የግል ጥበቃ አገልግሎት ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶች ላይ ያተኮረ ዛሬ መጋቢት 03/2012 የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ በተዘጋጀብት ወቅት ንግድ ተቋማት የሚቀጠሩ የጥበቃ ሰራተኞች መሳረሪ ይሰው እየተሰወሩ ስለመሆናቸው ተገለጸ፡፡በዕለቱ በቀረበው ጥናታዊ ፅሁፍ ላይም የግል ጥበቃ ሰራተኞች ለጥበቃ አገልግሎት የተሰጣቸውን መሳሪያ ይዞ የመጥፋት፣ ከዘራፊዎች ጋር በመመሳጠር ዝርፊያ የማካሄድ፣ስራ ቦታ ላይ ጠጥቶ መግባት እና በስራ ቦታ ላይ የመተኛት ችግሮች እንዳሉባቸው ተጠቅሷል።(ኢትዮኤፍኤም)
………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………..

የፌደራል ኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ከመጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ ፓስፖርት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ መስጠት ሊጀምር መሆኑን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር  ሙጅብ ጀማል ገለጹ፡፡ከዚህ ቀደም አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት ሁለት ወር ከ15 ቀን በላይ ይወስድ የነበረው ጊዜ ወደ አንድ ወር ዝቅ እንዲል ተወስኗል ሲሉም ሙጅብ አክለው ተናግረዋል።(ፈና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………..

ኢትዮጵያ በቄራ ኤክስፖርት ዘርፍ ዓለም አቀፍ የምግብ ጥራት ሽልማት አሸናፊ የሆነችው በሉና ኤክስፖርት ቄራ ሃላፊነቱ በተወሰነ የግል ማህበር አማካኝነት እንደሆነ ተገለጸ።ማህበሩ ከፍተኛ የምግብ ጥራት ደረጃ ሽልማትን በአሜሪካ በተካሄደ መርሃ ግብር ባለፈው ወር መጨረሻ ማግኘቱን አስታውቋል። (ኢዜአ)

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here