ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለኮቪድ19 ድንገተኛ ሁኔታ ዝግጅት የሚውል ገንዘብ እና ሌሎች አቅርቦቶችን የሚያሰባስብ ብሔራዊ የአቅርቦት አፈላላጊ ኮሚቴ አቋቁመዋል።
መንግሥት ጠቀም ያለ በጀት መደቦ የመጨረሻው አስከፊ ሁኔታ ቢከሰት ለመቋቋም የሚያስችሉ ግብአቶችን በማሰባሰብ ላይ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን ነገር ግን እንዲህ ያለው ጊዜ የእያንዳንዱን ግለሰብ አስተዋጽኦ የሚፈልግ ነው ተብሏል።
ተረጋግቶ አስተዋጽኦ ማድረግ’ን በቀዳሚነት ተግባራዊ በማድረግ የብሔራዊ ኮሚቴው አባላት የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለብሔራዊው የኮቪድ19 አቅርቦት ማሰባሰቢያ ለግሰዋል።



