ጠቃሚ ምክሮች ኮሮና ቫይረስን በተመለከተ ለሚዘግቡ ጋዜጠኞች

0
570

የጋዜጠኞች ምክር

ዓለም ዐቀፉ የምርመራ ጋዜጠኝነት ትስስር ከቀደምት የጤና ጋዜጠኛ፣ የተላላፊ በሽታዎች ባለሞያ እና የዓለም ዐቀፍ የጤና ደኅንነት ባለሞያው ቶማስ አብርሃም፣ ጋር ካደረገው ቃለ ምልልስ ላይ የተወሰደውን ይህንን ምክር ይመልከቱ። ቶማስ ‹‹የ ትዌንቲ ፈርስት ሴንቸር ፕሌጅ፡ ዘ-ስቶሪ ኦፍ ሳርስ›› የተሰኘውን በሳርስ ላይ የተዘጋጀው እና ‹‹ፖሊዮ፡ ዘ ኦዲሲ ኦፍ ኢራዲኬሽን›› የተሰኘውን በፖሊዮ ላይ የተዘጋጁት መጽሐፍት ደራሲ ናቸው።

በ13 ዓመቷ በሆንግ ኮንግ በሳርስ በሽታ ተይዛ የነበረችው እና ከበሽታው ከተረፈች በኋላም ሳርስ እና ኢቦላ ላይ ቀዳሚ ዘጋቢ ሆና ስታገለግል የነበረቸው ካሮላይን ቼን፣ በፕሮፑብሊካ ላይ የጤና ነክ ጉዳዮች ጸሐፊ ነች። በኮቪድ19 ላይ ባዘጋጀችው በዚህ ጽሑፏ ላይም ኮቪድ19ኝ በምንዘግብበት ወቅት ልንጠይቃቸው የሚገባቡ ጥያቄዎች ምንድን ናቸው የሚለውን ታስረዳለች።

ዘገባዎቻችን በግምት፣ በትንበያዎች እና በጣም በሚቀያያር መረጃ ላይ ቢመሰረቱም እንዴት ትክከለኛ ሆነው መቀጠል ይችላሉ የሚለውን እና ከምንም በላይ ግን እንዴት ራሳችንን ጠብቀን መዘገብ እንችላለን የሚለውን ታስረዳለች።

በጤና ጉዳይ ላይ ከ20 ዓመታት በላይ ልምድ ያካበተው ጆን ፖፕ ደግሞ ስዋይን ፍሉን በመዘገብ ወቅት ከግምት ውስጥ ልንከታቸው የሚገቡ 11 ምክሮችን ሲል አስነብቧል። ይህ ጽሑፍ ያካተታቸው ምክሮች ለኮቪድ19ኝም ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ። ምክሮቹም መሰረታዊ የሆኑ መረጃዎችን ይዞ መነሳት፣ በሽታውን በካርታ አስደግፎ ማዘጋጀት እና መረዳት፣ ነገሮችን በአጭር እና በቀላሉ ማስቀመጥ፣ ቅድመ መከላከል ላይ ማተኮር እና የምንጠቀማቸው ቃላት ላይ በትኩረት እና በጥንቃቄ መሥራት የሚሉ ናቸው።

የዓለማቀፉ የጋዜጠኞች ትስስር አይጄኔት ያዘጋጀው ኮቪድ19ኝን በምንዘግብበት ወቅት መተግበር ያለባቸው ጠቃሚ ምክሮች እንዲህ በአጭሩ ቀርበዋል፤

 

1/ አካባቢውን እና በመሬት ላይ ያለውን ሁኔታ በጥሞና በማስተዋል ከዘገባችን ጋር አጣጥሞ መተርጎም ያስፈልጋል፤

2/ ሁኔታውን በመዘገብ እንጂ ትንተና በመስጠት ላይ አለማተኮር፤

3/ ለምንሰጣቸው ርዕሶች ትኩረት መስጠት፤

4/ ሁሉም ቁጥሮች ትክክለኛ ያለመሆናቸውን ማስተዋል፤

5/ ዘረኛ የሆኑ የዘገባ ርእሶችን መቀነስ፤

6/ በተቻለ መጠን የተለያዩ እና ብዙ ሰዎችን ለማነጋገር መሞከር፤

7/ ባለሞያዎችን ቃለመጠይቅ የማድረጊያ ዘዴዎችን በደንብ ማጤን፤

8/ በጣም አስደማሚ አይደሉም በሚል አንዳንድ ዜናዎችን ላይ አለመዘናጋት

9/ ለዘገባዎች ገደብ ማስቀመጥ። አንደንዴ አርታኢዎችን አይሆንም ማለት ይልመዱ፤

10/ ሁኔታዎች በሚረጋጉበት ወቅትም ዘገባዎች መሥራትዎን ይቀጥሉ፣ አያቋርጡ፤

 

የዓለም አቀፉ የምርመራ ጋዜጠኞች ትስስር የባንግላዲሽ አርታኢ የሆኑት ሚራጅ አህመድ ቾውዱሪ  ያዘጋጁትን ፅሁፍ የትስስሩ የአፍሪካ ክንፍ በአማርኛ ካዘጋጀው የተወሰደ ነው፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ቀጣዩን ርእስ ይጫኑ ‹‹ጠቃሚ ምክሮች ኮሮና ቫይረስን በተመለከተ ለሚዘግቡ ጋዜጠኞች››

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here