የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በስምንት ወራት ከወጪ ንግድ 1.8 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱን አስታወቀ

0
453

በበጀት ዓመቱ ስምንት ወራት 2.3 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ በአፈፃፀም የተመዘገበው 1.8 ቢሊዮን ዶላር መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ይህም ዕቅዱን 79 በመቶ እንደሆነ ተገልጿል።

ይህ አፈፃፀም ከአምናው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወራት ከተገኘው 1.6 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ጋር ሲነፃፀር በ171 (10 %) ሚሊዮን ዶላር ገቢ ጭማሪ ማሳየቱን የንግድና ኢንዱሰትሪ ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አስታውቀዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ስምንት ወራት ከተያዘላቸው ዕቅድ በላይ አፈጻጸም ያስመዘገቡት የወጪ ንግድ ምርቶች አበባ፣አትክልትና ፍራፍሬ እና ጫት ናቸው፡፡ እንዲሁም የዕቅዱን ከ50% እስከ 90% ክንውን ያስመዘገቡ የወጪ ምርቶች ደግሞ ቡና ፣ የቅባት እህሎች ፣ ስጋ ፣ ጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ የጥራጥሬ ሰብሎች እና የቅመማ ቅመም ምርት ናቸው፡፡

በሌላ በኩል ከተያዘው ዕቅድ አንጻር በውጭ ምንዛሪ ገቢ ከ50 በመቶ በታች ዝቅተኛ ገቢ ያስመዘገቡ የወጪ ንግድ ምርቶች ቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ የቁም እንስሳት እና ወርቅ የወጪ ንግድ አፈጻጸም እንደሆነ ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የበጀት ዓመቱ ስምንት ወራት የወጪ ንግድ የአፈጻጸም ከአምናው ጋር ሲነጻጸር ዕድገት እንዳለ ቢያሳይም የሚፈለገውን ያህል እንዳልሆነ ተገልጿል፡፡ ይህንንም ለማሻሻል ስር ነቀል ለውጥ ማድረግ እንደሚገባ ዳይሬክተሩ አሳስበዋል ፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 75 ሚያዝያ 3 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here