አራት ድርጅቶች ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ጀመሩ

0
784

አራት የትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበራት በአዲስ አበባ ውስጥ ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ተገለጸ። በከተማዋ በሕዝብ ማጓጓዣዎች ላይ ሊፈጠር የሚችለውን መጨናነቅ ለመቀነስ ታስቦ የቀረበውን አገራዊ ጥሪ ተቀብለው ዘመን ባስ፣ ጎልደን ባስ፣ ሀበሻ ባስ እና የኛ ባስ አክሲዮን ማህበራት አውቶብሶቻቸውን በመመደብ አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።
በኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ምክንያት ርቀትን ጠብቆ ለመጓጓዝ የሚፈጠረውን የትራንስፖርት እጥረትና መጨናነቅ ለመቀነስ በማሰብ “ነፃ የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት ለአሳደገን ህዝብ” በሚል መሪ ቃል አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል።
በዚህም መነሻ መስቀል አደባባይ ሆኖ፥ መዳረሻ ቦታዎች ጦር ሀይሎች፣ አየርጤና፣ ሳር ቤት፣ መካኒሳ፣ ጀሞ፤ ተመላሽ በሃና ማሪያም ቃሊቲ፣ ከቃሊቲ ሳሪስ አቦ፣ ቦሌ፣ ሜክሲኮ ሳሪስ አቦ፣ ቦሌ፣ ሜክሲኮ፣ መገናኛ፣ ወሰን፣ ካራ፣ የካ አባዶ፤ ተመላሽ በመገናኛ፤ ቦሌ፤ ሳሪስ ቃሊቲ።
ከቃሊቲ በሳሪስ ስታዲየም- ሜክሲኮ – ሳሪስ – ቃሊቲ። ተመላሽ እስከ ሜክሲኮ፣ አራት ኪሎ፣ ስድስት ኪሎ፣ ሽሮ ሜዳ፣ፒያሳ አዲሱ ገበያ።
አስኮ መንገድ መድኃኒዓለም እነዚህን ዋና ዋና መንገዶችን መነሻና መድረሻ በማድረግ ስምሪቱ እንደ አካባቢው ትራንስፖርት እጥረት የሚስተካከል ሲሆን፤ ከሚያዚያ 1 ቀን ጀምሮ ላልተወሰኑ ቀናቶች በስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚሰጥ አክሲዮን ማህበራቱ አስታውቀዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 75 ሚያዝያ 3 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here