በኮቪድ 19 የሞተን ሰው ወደ ኢትዮጵያ ማጓጓዝ እንደማይቻል ተገለጸ

0
607

በኮሮና ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ህይወታቸው አልፎ አስከሬናቸውን ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት ወይም ለማጓጓዝ መሞከር ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑን የኅብረተሰብ ጤና ኢንቲትዩት አስታወቀ። ኢንስቲትዩቱ ለኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን በጻፈው ደብዳቤ እንዳስታወቀው ከየትኛውም አገር ወደ ኢትዮጵያ በኮቪድ 19 ተጠቅቶ ህይወቱ ያለፈ ሰውን ማጓጓዝ ከበሽታው ጸባይ አለመታወቅ ጋር ተያይዞ አደገኛ ሁኔታን ሊፈጥር ይችላል ሲልም አስታውቋል።

በአውሮፕላን በሚጓጓዝበት ወቅትም ሰዎች ጋር ንክኪ ሊፈጠር ስለሚችል በቀላሉ ጤነኛ ሰዎችን ሊበክል እደሚችል እና ገና በሳይነሳዊ ዘዴ የበሽታው መተላለፊያ በእርግጠኝነት ባለመታወቁ ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ በረራዎች በኮቪድ 19 የሞቱ ሰዎችን መጫን እንደሌለባቸው ለባለስልጣኑ በደብዳቤ አስታውቋል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት። ከዚህም ጋር ተያይዞ ባለስልጣኑ ለኹሉም የአየር መንገዱ ኦፕሬተሮች መልዕክቱን እንዲያሰተላልፍም አሳስቧል። ኢንስቴትዩቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ቸምሮ በአገሪቱ የትኛው መውጫ እና መግቢያ በሮች ላይ የምርመራና የልታ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም አስታውቋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 75 ሚያዝያ 3 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here