ሳኖፊ እና ጅኤስኬ የተባሉ ኹለት ኩባንያዎች ከዚህ ቀደም ባልታየ መንገድ የኮቪድ 19 ክትባትን በጋራ ለማምረት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታወቁ። ሳኖፊ የተሰኘው ኩባንያ ኤስ ፕሮቲን የተሰኘ እና የሰውነትን የመከላከል አቅም እንዲጨምር የሚያደርግን ንጥረ ነገር ሲያመርት ይህ ንጥረ ነገርም ከቫይረሱ ዘረ መል ጋር ተቀራራቢ እንደሆነ አስታውቋል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ ጂኤስኬ የተባለው ኩባንያ ደግሞ በጠለቀ ቴክኖሎጂ አበርክቶ በክትባት ውስጥ የሚያስፈልገውን የፕሮቲን መጠን በማመጣጠን ረገድ ከፍተኛ ስራ እንደሚሰራም ታውቋል። በኹለቱ ኩባንያዎች ጥምረት ይሰራል ተብሎ የሚጠበቀው ክትባት በፈረንጆች 2020 ኹለተኛ አጋማሽ ላይ የመጀመሪያው ዙር የክሊኒክ ሙከራዎች የሚከናወኑ ሲሆን በሙከራውም አመርቂ ውጤት ከተገኘ እና አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ ካለፈ በ2021 ኹለተኛው መንፈቅ ተሰርቶ እንደሚጠናቀቅ ታውቋል።
ኹለቱ ኩባንያዎች የጋራ ግብረ ኃይል ያቋቋሙ ሲሆን የዓለም የክትባት ዳይሬክተር ዴቪድ ሎይው በምክትል ሊቀመንበርነት ግብረ ኃይሉን እንደሚመሩት ተገልጿል።
ሳኖፊ ኩባንያ የስይነሳዊ ግኝቶችን ወደ ሰው ልጆች የጤና አጠባበቅ በመቀየር ሰፊ ልምድ ያለው ዓለም አቀፋዊ ኩባንያ ሲሆን በ100 አገራት በመንቀሳቀስ 100 ሽሕ ሰዎችን ሊድኑ አይችሉም ከሚባሉ እና አልፎ አልፎ በውስን ሰዎች ዘንድ የሚከሰቱ በሽታዎችን በማከም ይታወቃል።
በሌላ በኩል ደግሞ ጂኤስኬ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም ከሚባሉ ክትባት አምራች ኩባንያዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን የሰዎችን የዕድሜ ጣሪያ በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ ርብርብ ከሚያደርጉ ድርጅቶች ተርታም ይመደባል።



