ከ11 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ሰባት መንገዶችን ለመገንባት የሚያስችል ውል ተፈረመ

0
729

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ከ11 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ሰባት መንገዶችን በአስፋልት ደረጃ ለመገንባት የሚያስችል የውል ስምምነት ፊርማ ማከናወኑን አስታወቀ ፡፡

ሰባቱ የተፈረሙት መንገዶች በጥቅሉ 509.11 ኪ.ሜ እርዝማኔ ያላቸው ሲሆን ለግንባታቸው የሚውለው ከ11 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚሸፈነው በኢትዮጵያ መንግስት መሆኑም ታውቋል ፡፡

የመንገድ ውል ስምምነት ፊርማ የተከናወነባቸው መንገዶችንም ባለስልጣኑ በዝርዝር ያሳወቀ ሲሆን እነሱም

  1. ደበረብርሃን – ደነባ -ለሚ መገንጠያ እና ጅሁር -ደነባ
  2. ፊቅ – ሰገግ – ገርቦ ደነን (ሎት ሶስት. ዮአሌ-ደነን )
  3. ሁምቦ – ጠበላ – አባያ
  4. ዳዬ – ግርጃ – ክብረመንግስት (መልካደስታ) እና መለያ – መጆ መገንጠያ
  5. ጅግጅጋ – ገለለሽ – ደገሃምዶ -ሰገግ (ኮንትራ ሁለት እና ሶስት )
  6. ሀወላቱላ-ወተራራሳ-ያዩ-ውራቼና
  7. ዛላምበሳ – አሊቴና- መረዋ – እዳጋሃሙስ ( ሎት አንድ. ዛላምበሳ – አሊቴና መገንጠያ ) ናቸው

መንገዶቹን ለመገንባት ጨረታውን አሸንፈው ከባለስልጣኑ ጋር የውል ስምምነት ፊርማ ያደረጉት ተቋራጮች ስድሰቱ አገር በቀል ሲሆኑ የተቀረው የውጭ ስራ ተቋራጭ ድርጅት መሆኑንም ባለስልጣኑ ያስታወቀ ሲሆን ተቋራጮቹ የተረከቧቸውን መንገዶች ገንብቶ ለማጠናቀቅ ከሶስት ዓመት እሰከ አራት አመት የጊዜ ገደብ እንደተሰጣቸውም ጨምሮ ገልፆል ፡፡

በአሁኑ ወቅት መንገዶች የሚገኙበት  ደረጃ ጠጠር ሆኖ ለእንቅስቃሴ አመቺ ያልሆነ ሲሆን በቀጣይ ደረጃቸው ወደ አስፈልት የሚያድግ ይሆናል ፡፡
የመንገዶቹ የጎን ስፋት በገጠር 7 ሜትር በከተማ ደግሞ ከ 10 ሜትር እንደሚኖራቸው ይጠበቃል ፡፡

በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ሀብታሙ ተገኘ የመንገዶቹ ግንባታ ሲጠናቀቅ ከዚህ በፊት በየአካባቢው የነበረውን የትራንስፖርት ችግር በመቅረፍ የአካባቢው ህብረተሰብ በቀላሉ ወደ ፈለገው ቦታ የሚንቀሳቀስበትን ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ብለዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ጨምረውም ለወጣቶች የስራ ዕድል እንዲፈጠር በማስቻል ፣በየአካባቢው የሚገኙ ትንንሽ መንደሮችና ከተሞችን እድገት ከማፋጠን እንዲሁም የጤና ፣ የትምህርት እና ሌሎች የማህበራዊ አገልግሎት ተቋማት እንዲስፋፉ ከማድረግ አንፃር የእነዚህ መንገዶች መገንባት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክትም ገልጸዋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here