ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ከደቡብ ክልል የዞን አመራሮች ጋር ውይይት አደረጉ

0
1039

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከደቡብ ብሔሮች፣ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል የዞን አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ውይይቱን አስመልክተው በፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት “የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል በብዙ የተፈጥሮ እና የባህል መስህቦች የታደለ ነው”። እነዚህን መልካም ጎኖች ለመጠቀም በጋራ ከሠራን፣ ክልሉ ለሌሎች የሚተርፍ የልማት ማዕከል እንደሚሆን ለበርካታ ጊዜያት መናገራቸውንም አስታውሰዋል።

“ባለፉት ሁለት ዓመታት፣ ወደ ክልሉ በተደጋጋሚ በመጓዝ ለማኅበረሰብ ልማት በእጅጉ ስለሚያስፈልጉ ጉዳዮች ከአንደበታቸው አድምጫለሁ፤ ሁሉንም መሠረታዊ ፍላጎቶች በአንድ ጊዜ ለማሟላት የሚቻል ባይሆንም፣ በዚህ ወቅት ዐበይት የመሠረተ ልማት፣ የኢንቨስትመንት እና ተያያዥ ሥራዎች ተከናውነዋል” ሲሉም ገልፀዋል።

በዛሬው እለትም ከክልሉ የዞን አመራሮች ጋር በነበራቸው ውይይት፣ በደቡብ ክልል ባለ ብዙ ገጽ ዕድገት እና ዘላቂ ሰላም እንዲኖር የአስተዳደራዊ መዋቅር መርኆውን ቅድሚያ ሰጥቶ መመልከት አስፈላጊ እንደ ሆነ መስማማታቸውንም አስታውቅዋል።

በዚህ ውይይት፣ በዝርዝር ሊታዩ የሚገባቸው ሌሎች ጉዳዮችም ተነሥተዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ፥ “ጉዳዮቹ የበለጠ ዳብረው ተመልሰን እንድንወያይባቸው ስምምነት ላይ ደርሰናል” ብለዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here